ጎበዜ ደርሶ / Gobezé Derso:
![]() |
“በህግ ከሄደች በቅሎዬ ያለ ህግ የሄደች ጭብጦዬ” |
![]() |
ጎበዜ
ከሲታ፣ ጠይም የቆሎ ተማሪ፣ ደበሎውን እንደለበሰ፣ በትሩን አጥብቆ ይዞ አኩፋዳውን በእጁ አንጠልጥሎ፣ በረባዳማው ሰርጥ በአእዋፋት
ድምፅ ተከቦ የልጅነት ፍቅሩን አለሜን ለሰባት ዓመታት ይፈልጋታል፣ ![]() |
ምነው የበላሽ ጅብ አልጮህ አለ?
|
Gobezé is a poor, peace-loving, young man of 25, a brilliant student who dedicated his whole life to Sem ina Werq riddles (literally translated to “Wax and Gold riddles”, which are riddles with dual meaning). He was betrothed to Alemé at a young age, and lived with and served her family as a shepherd. But the love of his life.
_________________________________________________________________________________
አለሜ እሸቱ/ Aleme Eshete
![]() |
ጋሻዬ ይዘኸኝ ጥፋ!
|
![]() |
ተሜ!
|
አለሜ - የደም ገንቦ፣ አይን አፋርና ለግላጋ የቤት እመቤት፣ ያደፈ ቀሚስ ለብሳ፣ ወገቧን በመቀነት አስራ
“አንቺ ዶሮ ባልሽ ማነው” የልጅነት ዜማዋን እያንጎራጎረች፣ ደጅ ደጁን ታያቸች፣ ተሜን እየጠበቀች፡፡
![]() |
ምነው ምነው ልቤ ካንተው ነው!
|
Alemé is a wise, beautiful, shy but courageous 23-year-old woman who is a victim of the tradition of abduction marriages. Although she lives with her abductor for seven years, her heart always longs for Gobezé.
“አንቺ
ዶሮ ባልሽ ማነው፣
አውራ ዶሮ፣
ምን ሊያበላሽ፣
ተበድሮ፣
ምን ሊከፍል፣
መሬት ጭሮ፣
መሬት ሲጭር፣
እዛው ፍንችር
የፍንጥሩ
ቅቤ ንጥር”
አውራ ዶሮ፣
ምን ሊያበላሽ፣
ተበድሮ፣
ምን ሊከፍል፣
መሬት ጭሮ፣
መሬት ሲጭር፣
እዛው ፍንችር
የፍንጥሩ
ቅቤ ንጥር”
__________________________________________________________________________________
ጎንጤ ጥጋቡ/ Gobeze Tigabu
ጎንጤ ደልዳላ ሰውነት ያለው ቁጡ ጭቃ ሹም ገበሬ፣ ከሚሽቱ አለሜ ጋር የተኛውን የቆሎ ተማሪ ሊፋለምና ቆለጡን ሊያስቀጠቅጥ ምሎ ተገዝቶ አድብቶበታል፡፡ “የተማሪ አባይ የደበሎ ተባይ ቢገላጥጡት አይታይ፣ አንት የደብተራ አስመሳይ”
Gobezé is a 45-year-old local judge, rich farmer and landlord who abducts the young girl, Alemé. He is invincible court debater, aloof but well-respected. He is filled with pride and with eagerness to get Gobezé punished in the royal court after he catches Gobezé in bed with his wife.
ንግስተ ነገስታት ዘውዲቱ ምንሊክ/ Queen of Kings, Zewditu Minilik:
ልዕልት ዘውዲቱ ምንሊክ፡- ጠይም፣ 40ዎቹ መጀመሪያ ላይ ያለች፣ አጭር፣ ሞላ ያለ ፊትና ገራገር አይኖች
ያሏት፣ያለፍላጎቷ ከዙፋን የተቆራኘች፣ ከባለቤቷ ራስ ጉግሳ ወሌ ተለይታ በሃሳብ የምትዋትት፣ በጎበዜና አለሜ ፍቅር የራሷን ጉዳት
የተመለከተች፣ ቅን ፈራጅ፣
“በንፁህ ላይ ሲፈርዱ፣ ከበድ ላም ሲያርዱ ሆድ መርበድበዱ…ዘውዲቱ ትሙት”
![](https://blogger.googleusercontent.com/img/b/R29vZ2xl/AVvXsEjWGmDt9GWEgoLV9gM5mPUv_NM91mjSaYbcVis7n8yNOZQ6Dg80P4dlti3iQ8iyQroLA22KgMYvi6_oayHYW48Xyew8M-TK95PK4KanSQx3VindDWJTlM5uj3pW_BxelmS2aoPJdIotXtyg/s320/NIGIST+ZEWDITU+3.jpg)
አፈንጉስ ታረቀኝ/ Afenigus Tarekegn
አፈንጉስ ታረቀኝ:- በጥሩ
እጀ ጠባብና ካባ የተሽቀረቀሩ፣ ባለግርማ፣ደልዳላ፣ የቀይ ዳማ፣ ፍንጭታም ኮስተር ያለ ግንባር ያላቸው መሰሪ መኳንንት፡፡
በችሎት ከጎበዜ ይልቅ ለጭቃ ሹሙ ጎንጤ የሚያደሉ ጥቅመኛ ፡፡
“ጉፋያ ብቻ ነው ትረታዋለህ፣
ሙግት አያውቅም፣ ደጋግመህ ልታስቀጣው ትችል ነበር”
![](https://blogger.googleusercontent.com/img/b/R29vZ2xl/AVvXsEiRvBfghyz6FSi3sR_vFnIh0tgc4anhZXFEWhLZRLoZbVQBlJ4IjAON6R6ap22zA7pKvoJn6VEPn-ID17fAU8InUY-9E6SK341FgRSx5xfgT_AEYttpJq0ufrB-h9vCgi65i7V9d9h9uBKm/s400/WIDE+NIGIST+CHILOT.jpg)
መሪጌታ በእውቀቱ ቦጋለ/ Priest Bewketu Bogalé:
መሪጌታ በእውቀቱ ቦጋለ፣ መጣጣና ጠይም ፊታቸው፣ ከራሳቸው ላይ የተቆለለው ትልቅ የክህነት ጥምጣም፣ ሰውነታቸው ላይ የደረቡት
የሰፋቸው ጥቁር ካባቸው ይበልጥ ከሲታ አድርጎአቸው ተማሪዎቻቸው ፊት ቆመው ቅኔ ያስተምራሉ፣ ጎበዜ ትጉህ ነገር ግን አመፀኛ
ተማሪያቸው ነው፡፡
“ጎበዜ የቅኔ ወኔህን አሳየን፣
ዕጣነ ሞገርህን አሰማን፣
ሁላችን ቅኔ ስትዘርፍ መስማት እንሻለን…
የፍቅር ቅኔ፣
የፍትህ ቅኔ”
![](https://blogger.googleusercontent.com/img/b/R29vZ2xl/AVvXsEhlCcjUJUIhL-iskEVGJHXVrB1fpzlLHEcrZ5nw8WE8v2kJSlzqYSWBE3XKKGWhBZB7KSFQ_-sAh36-7vWRg7sGI5ehDy_cSSq7hfdF2UD8x0Af9Jz5ICujg0NQWBhgyhK_XrD5ishRC-ex/s320/WIDE+GONTE+%2526+YENETA.jpg)
ሸፍታው አረሩ/ Areru the Bandit:
“ህልጊዜ አዋቂዎች ብልጥ
እናንተ ብቻ፣ እኛ መች አጣነው ባዶውን ኮርቻ”
![](https://blogger.googleusercontent.com/img/b/R29vZ2xl/AVvXsEilcSiVBTzguHIdE__jb2nDrl5KLGr8hYONp64uPxhanvxUrmXNQCbFD03cfvn0u5CCGN2C-9bYv66JpSGKgTyYAo1BwBIdrJ1GezgywjgV5atjJKu1xT3bbcsTOES1EPZlHTI6ekk9kEQ7/s320/ARERU+GIFT+TO+GOBEZE.jpg)
Areru is a bandit and a wild man, although he is initially against Gobezé trusting the justice system, he is encouraged enough by Gobezé’s determination to get justice that he decides to stand before the royal court and defend Gobeze.
No comments:
Post a Comment